
እንኳን ወደ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ ይፋዊ ድረ-ገጽ በደህና መጡ !


ክቡር አቶ ፋጂዮ ሳፒ ወትራሻ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ
እንኳን ወደ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ ይፋዊ ድረ-ገጽ በደህና መጡ!!! የፕላንና ልማት ቢሮ የክልሉን ረቂቅ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ማርቀቅና ማበልጸግ፣ የኢኮኖሚ ጥናትና ምርምር በማካሄድ የልማት ዕቅዶችን በማዘጋጀት፣ አፈጻጸምን ለመለካት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አመለካከቶችን በማዘጋጀት፣ አጠቃላይ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊና የቴክኖሎጂ ልማት ማዕቀፎችን በመፍጠርና በመተግበር በኩል ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡
ስለ ክልላዊ አጠቃላይ የምርት ዕድገት መጠን፣ በኢኮኖሚ ሴክተሮች የሚጨመሩት የእሴት ዕድገት መጠን እና ከጠቅላላ ምርት ድርሻቸው ላይ መረጃ ያገኛሉ። ከክልላዊ እቅድ እና ሪፖርቶች ጋር የተያያዙ ጠቃሚ ግብዓቶችን፣ የአሰራር ደንቦችን እና መመሪያዎችን እና የተለያዩ ዘርፎችን የሚመለከቱ ማሻሻያዎችን ለምሳሌ እንደ ማህበራዊ ደህንነት፣ የስነ ሕዝብ አወቃቀር እና የአካባቢ ዘላቂነት እና ሌሎችንም ልናቀርብልዎ ተዘጋጅተናል፡፡
የክልሉን ማህበራዊ ፣እኮኖሚያዊና ዴሞግራፊየዊ መረጃጃዎችን በማሰባሰብ፣በማደራጀትና በመተንተን ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ መረጃዎችን ለፖሊሲ ቀራጮች፣ለዕቅድ አዉጭዎች፣ለፕሮጀክትና ፕሮግራም አዘጋጆች፣ለትምህርትና ምርምር ሥራዎች አዘጋጅቶ በማቅረብ የክልሉን ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ልማት የልማት እንቅስቃሴና መልክዓ ምድራዊ ገጽታን የሚያሳይ አትላስ ካርታ ማዘጋጀት ተቀዳሚ ተግባሩ ነዉ፡፡
የሥነ-ህዝብ ፖሊሲን እንዲያስፈፅም ተልዕኮ ከተሰጣቸዉ ክፍሎች አንዱ ሲሆን ከተሰጠዉ ተግባርና ኃላፊነት አንጻር የክልሉን ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ዴሞግራፊያዊ መረጃዎችን፣ መነሻ በማድረግ የሥነ-ህዝብ ምክር ቤት በማቋቋም፣ የሥነ-ህዝብ ጉዳዮችን በሚመለከታቸዉ ሴክተሮች የልማት ዕቅድ ዉስጥ በማካተት የድጋፍና ክትትል ተግባሮችን የማከናዎን ሥራዎችን ይሰራል፡፡
በዚህ ድረ-ገጽ ላይ የክልል ልማትና የመልካም አስተዳደር ዕቅዶች፣ የአፈጻጸም ሪፖርቶች፣ የፕሮጀክት ዕቅዶችና የአፈጻጸማቸው ሁኔታ ወቅታዊና የተገመገሙ መረጃዎችን ያገኛሉ። በተጨማሪም በክልሉ ውስጥ ያሉትን የአስተዳደር እርከኖች ካርታዎች፣ በክልሉ ውስጥ የመሠረተ ልማት አውታሮች ስርጭት፣ የክልሉ ሙሉ መገለጫ እና ለበጀት ቀረጻ ጥቅም ላይ የሚውሉ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ስለዚህ ድረ ገጻችንን እንድትጎበኙ እና ያቀረብነውን መረጃ እንድታገኙ እንጋብዛለን። ይዘቱን እና ድህረ ገጹን በተመለከተ ለሰጡን አስተያየቶች እና ጥቆማዎች እናመሰግናለን።

አቶ ሳምሶን አድማሱ ወልደሚካኤል
ምክትል ቢሮ ኃላፊ እና የልማት መረጃ ስርዓት አስተዳደር እና የስነ-ህዝብና ልማት ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ
እንኳን ወደ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦችክልላዊ መንግስትፕላንና ልማት ቢሮ ይፋዊ ድረ-ገጽ በደህና መጡ!!!
በፕላንና ልማት ቢሮ ዉስጥ የልማት መረጃ ሥርዓት አስተዳደርና ስነ-ሕዝብ ልማት ጉዳዮች ዘርፍ አንዱ ሲሆንከተሰጠዉ ተግባርና ኃላፊነት አንጻር በክልሉ ሥነ-ህዝብ ፖሊሲን ያስፈጽማል፤የክልሉን ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ዴሞግራፊያዊ መረጃዎችን መነሻ በማድረግ የአምስት ዓመት የሥነ-ህዝብ ፕሮገራም ሰነድ በማዘጋጀት በስነ-ህዝብ ምክር ቤት ያስጸድቃል፡፡የሥነ-ህዝብ ጉዳዮችን በሚመለከታቸዉ ሴክተሮች የልማት ዕቅድ ዉስጥ በማካተት የድጋፍና ክትትል ተግባሮችን የማከናዎን ሥራዎችን ይሰራል፡
የክልሉን ማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊና ዴሞግራፊየዊ መረጃጃዎችን በማሰባሰብ፣በማደራጀትና በመተንተን ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ መረጃዎችን ለፖሊሲ ቀራጮች፣ለዕቅድ አዉጭዎች፣ለፕሮጀክትና ፕሮግራም አዘጋጆች፣ለትምህርትና ምርምር ሥራዎች አዘጋጅቶ በማቅረብ የክልሉን ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ የልማት እንቅስቃሴና መልክዓ ምድራዊ ገጽታን የሚያሳይ አትላስ ካርታ ማዘጋጀት ተቀዳሚ ተግባሩ ነዉ፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የክልሉን ዳታ ቤዝ ያዘጋጃል፣ያስተዳድራል እንዲሁም የቢሮዉን ድረ-ገጽ ያለማል፣ያስተዳድራል የተለያዩ ዘመናዊ ቴክኖሎጅዎችን በማላመድ ጥቅም ላይ እንዲዉል ያደርጋል፡፡
በዚህ ድረ-ገጽ ላይ የክልሉ ልማትና የመልካም አስተዳደር ዕቅዶች፣ የአፈጻጸም ሪፖርቶች፣ የፕሮጀክት ዕቅዶችና የአፈጻጸማቸው ሁኔታ ወቅታዊና የተገመገሙ መረጃዎችን ያገኛሉ። በተጨማሪም በክልሉ ወይም በዘርፉ ውስጥ ያሉትን የአስተዳደር እርከኖች ካርታዎች፣ በክልሉ ውስጥ የመሠረተ ልማት አውታሮች ስርጭት፣ የክልሉ ሙሉ መገለጫ እና ለበጀት ቀረጻ ጥቅም ላይ የሚውሉ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ስለዚህ ድረ ገጻችንን እንድትጎበኙ እና ያቀረብነውን መረጃ እንድትጠቀሙ እየጋበዝን ይዘቱን እና ድህረ ገጹን በተመለከተ ለሰጡን አስተያየቶች እና ጥቆማዎች በዘርፉ ስም እናመሰግናለን።
አቶ ሳምሶን አድማሱ ወልደሚካኤል የዘርፉ ዋና ኃላፊ

አቶ ሚሊዮን አደሞ ዱንቢሎ
ምክትል ቢሮ ኃላፊ እና ማክሮ ኢኮኖሚ ዕቅድ ዝግጅት እና ክትትል ዘርፍ ኃላፊ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ አጠር ያለ መግለጫ እና በክልሉ ውስጥ የሚገኙ የተፈጥሮ መስህቦች በፎቶ !

የክልሉ ፕላን ቢሮ በክልሉ ም/ቤት የክልሉን አስፈፃሚ መ/ቤቶች እንደገና ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 33/2016 የፋይናንስና ፕላን ቢሮ በጥምረት ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በሚል ጥምር ሲያሜ በቢሮነት ተቋቁሞ ከህዳር 2014 እስከ 2016 በጀት ዓመት መጠናቀቅያ ድረስ በፋይናንስ ስር የቆየ ሲሆን በተሻለ አፈፃፀም የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት ታስቦ ለ2017 በጀት ዓመት እንደገና በአዋጅ ቁጥር 33/2016 ፕላን በቢሮ ደረጃ ተሻሽሎ ተቋቁሟል፡፡ ቢሮዉ የክልሉን አጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታዎችን በማጥናት ማነቆ የሆኑ ችግሮችን በመለየት የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ማመላከትና የክልሉን ማህበራዊ' ኢኮኖሚያዊና መልካምድራዊ መረጃዎች ጥራቱን በጠበቀና በአስተማማኝ ሁኔታ በማዘጋጀት ለውሳኔ ሰጪ አካላት፣ ለፖሊሲ አውጪዎች፣ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ለጥናትና ምርምር ተቋማት ያቀርባል፡፡
በክልሉ ተግባራዊ የሚደረጉ የካፒታል ፕሮጀክቶች የተጣለባቸውን ግቦች በማሳካት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችል ጠንካራ የክትትልና ግምገማ ስራዎችን ተግባራዊ ማድረግ፣ የክልሉ የህዝብ እድገት ምጣኔ ከክልሉ ኢኮኖሚ የዕድገት ምጣኔ ጋር እንዲጣጣም ማድረግና በሥነ ህዝብና ልማት ዙሪያ ለማህበረሰቡ ሰፊ የትምህርትና ቅስቀሳ ስራዎችን መተግበርና በክልሉ የሚገኘው የተፈጥሮ ሀብትን በአግባቡ በመጠቀም ታዳሽ በሆኑ የተፈጥሮ ሀብት ላይ በማተኮርና ታዳሽ ያልሆኑ ሀብቶችን ቀጣይ ትውልድን ታሳቢ በማድረግ በተመጣጣኝ መልኩ ጥቅም ላይ እንዲውሉ በማድረግ የክልሉ ኢኮኖሚ ዕድገት ቀጣይነትና ዘላቂነት እንዲኖረው ማረጋገጥ በመሠረታዊ ተልዕኮዎች ውስጥ የተካተቱ ናቸው፡፡






በማኀበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ጥናቶችን በማካሄድና የፖሊሲ ማሻሻያ ሀሳቦችን በማመንጨት፣ ግልፀኝነትና ተጠያቂነት በሰፈነበት አሰራር ዘመናዊ የልማት ዕቅድና መረጃ፣ በመዘርጋት፣የልማት አጋሮችን በማስተባበርና የሕዝብ ቁጥር ዕድገት ከኢኮኖሚ እድገት ጋር እንዲጣጣም በመስራት በክልሉ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማት እንዲረጋገጥ ማስቻል፡፡
ኢኮኖሚያዊና ማኀበራዊ ዕድገትን በማስፈን የክልሉ ሕዝብ ከድህነት ተላቆ“ኢትዮጵያ አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት”ሀገራዊራ ዕይ በ2024 ዓ/ም ተሳክቶማየት፡፡
- ቆጣቢነት
- ወቅታዊና አስተማማኝ መረጃ
- ፍትሃዊነት
- ውጤታማነት
- ግልፀኝነትና ተጠያቂነት
- ተቆርቋሪነት
- ቀልጣፋ አገልገሎት
- በእቅድ መመራት
- ሕጋዊነት
Location
MIZAN-AMAN
ETHIOPIA
Pages
Follow us


It is very good work keep it up
Thank you
it is good
በካፕታል ፕሮጀክቶች ዙሪያ ወጥ የሆነ አሰራር መመሪያ እስከ ወረዳ ተዘጋጅቶ ብላክልን