አቶ ሽመልስ ካሌብ ናፋ
የሰዉ ሀብት አስተዳደር ዳይሬክተር
የሰው ሀብት ሥራ አመራር ዳይሬክተር ዋና ዋና ተግባራት
የዳይሬክቶሬቱን ተግባራት ያቅዳል፣ ያደረጃል፣ ይመራል፣ይከታተላል፣ ይደግፋል፣ ይወስናል ይቆጣጠራል፣ የስራ አፈጻጸም ይገመግማል፣ ክፍተቶችን ይለያል፣ ያበቃል፣
ከዘርፉ ስትራቴጂክ ዕቅድ የተመነዘረ ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣
· የቢሯችን ሠራተኞች ጡረታ መለያ ቁጥር ማዉጣት ፣ ሠራተኞች በሥራ ገበታቸው ላይ ዕለት በዕለት መገኘታቸው ቁጥጥርና ክትትል ማድረግ ፣ የሥራ ልምድ፣ የዋስትና ድጋፍና የአገልግሎት ማቋረጥ ደብዳቤ አዘጋጅቶ መሰጠት
ለተቋም ሠራተኞች መንግሥት በወጣው የምዘና ስርዓት መሠረት በየወቅቱ እንዲመዘኑ ያደርጋል፣ በምዘናው ውጤት መሠረትም ቀጣይ ተግባራትን ያካናውናል፣
በተቋሙ የበላይ ኃላፊዎች በሚሰጠው የሥልጣን ውክልና መሠረት በሰው ሃብት ሥራ አመራርና አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጣል፣ ወይም የሚሰጡ ውሳኔዎችን ተግባራዊነት ይከታተላል፣
በመንግሥት ሠራተኞች መመሪያዎችና ደንቦች መሠረት ለተቋም የቅጥር፣ የደረጃ ዕድገት፣ ዝውውር፣ የድስፕሊን፣ የቅሬታ ማስተናገጃና እንዲሁም ሌሎች አግባብነት ያላቸው ኮሚቴዎች እንዲቋቋሙና ተግባራዊ እንዲሆኑ ይከታተላል፣
አዲስ ለሚቀጠሩ ሠራተኞች ስለ መንግሥት መመሪያዎችና ደንቦች እንዲሁም ተቋሙ ስለተቋቋመበትና ስለሚጠበቅበት ውጤት እንዲሁም ስለ መሥሪያ ቤቱ ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች ኃላፊነት የማስተዋወቂያ ስልጠና (`Inducation) እንዲሰጥ በማድረግ ወደ ሥራ እንዲሰማሩ ያደርጋል፣
የዳይሬክቶሬቱን ወቅታዊ የሥራ አፈጻጸም ለበላይ አካል ሪፖርት ያቀርባል፣
አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ለተቋም የሰው ሀብት ሥራ አመራርን የተመለከቱ መመሪያዎች እንዲከለሱና አዳዲስ ጥናት እንዲጠኑ ያደርጋል፣ የጥናት ውጤቶችን ይገመግማል፣
ለሥራ መደቦች የሥራ ትንተና ተከናውኖ የሥራ ዝርዝር መግለጫ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣
መልካም ተሞክሮዎችን በማጣጣም ዳይሬክቶሬቱ የሚመራበትን አዳዲስ አሰራሮች በመቀመር እንዲቀመር በማድረግ፣ በመገምገም የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፣ ያስፋፋል፤
የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ ሰርኩላሮችና አግባብነት ያላቸው መመሪያዎችን ተፈጻሚነታቸውን ይከታተላል፣
በተቋም ውስጥ ሜሪቲን የተከተለ የሰው ሀብት ምልመላና መረጣ እንዲከናወን ያደርጋል፣
በተቋም ውስጥ ልዩ ልዩ ጥቅማ ጥቅሞችና አገልግሎቶች ሳይዛቡ ሥራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፣
ደረጃውን የጠበቀ የሰው ሃብት የሥራ አካባቢ ደህንነትና ጤንነት ጥበቃ እንዲከናወን ያደርጋል፣
የሠራተኛ የግል ማህደሮች ተሟልተውና ዘመናዊ ሆነው እንዲያዙ ክትትል ያደርጋል፣
በተዋረድ ከሚገኙ ተቋማት በሰው ሃብት ሥራ አመራር ዙሪያ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች የአሠራር ሥርዓቱን መሠረት በማድረግ ምላሽ እየሠጠ ፣ አፈፃፀሙን ይገመግማል፣ትክክለኛነቱን ያረጋግጣል፣
የሰው ኃይል እቅድ መረጃዎች እንዲሰበሰቡ፣ እንዲደራጁ ተተንትነው እንዲጠናቀሩ ያደርጋል፣ የመረጃዎችን ትክክለኝነት ያረጋግጣል፣ ለሚመለከተው አካል ያስተላልፋል፣
በደረጃው ለተፈቀዱ የስራ መደቦች የሰው ኃይል ስምሪት ፈተናዎችን ያዘጋጃል፣ በሚመለከታቸው የስራ ክፍሎችም እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ ይፈትናል፣ እንዲፈተኑ ያደርጋል፣ ያርማል፣ እንዲታረም ያደርጋል፣ መረጃዎቹን በዘመናዊ የመረጃ ዘዴ /በሃርድና በሶፍት ኮፒ/ ተደራጅተው እንዲያዙ ያደርጋል፣
