በፕላንና ልማት ቢሮ የመረጃ አስተዳደር ሥርዓትና ሥነ-ህዝብ ጉዳዮች ዘርፍ የሥነ-ህዝብ ልማት ትምህርትና ቅስቀሳ ዳይሬክቶሬት

አቶ መንገሻ ኦይዲን ሺካ
የስነ ሕዝብ ልማት ትምህርትና ቅስቀሳ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
ዓላማዉ
ዋና ዓላማዉ የህዝብ ቁጥር ምጣኔን ከኢኮኖሚያዊ ከማህበራዊ እንድሁም ከተፈጥሮአዊ የሥነ-ምህዳር አቅም ጋር በማጣጣም ከኢኮኖሚ አቅም ጋር የተጣጣመ የህዝብ ቁጥር እድገት እንዲኖር ማስቻል፣ ነዉ፡፡
1.1 ሥነ ህዝብ ልማት ትምህርትና ቅስቀሳ ዳይሬክቶሬት ተግባራት
1.1 የክትትልና ማስተባበር ተግባር
- የረጅምና፣መካከለኛ (የ10 እና 5 ዓመት) የሥነ ህዝብ ፕሮግራም ሰነድ ዝግጅት ማዘጋጀት የታችኛዉ መዋቅር በውቅቱ መዘጋጀታቸውን መረጋገጥ፡፡
- የተለያዩ ሥነ ህዝብ ጉዳይ ደንብና መመሪያዎችን መዘጋጀት፤አፈጻጸማቸዉን መከታተል፡፡
- ከሚመለከታቸው ባለድርሻ ተቋማት በአጭር፣ በመካከለኛና በረዥም ጊዜ የስነ ህዝብ ጉዳይን በዕቅዳቸው ውስጥ ማካታተቸውን ይከታተላል፣ያረጋግጣል፤እንዲያካትቱ ያደረግል፡፡
- የሚነደፉት የሥነሕዝብ ፕሮግራሞች፤ ፕሮጄክቶችና ዕቅዶች ፖሊሲው ላይ ከተቀመጡት ስትራቴጂዎች ጋር የተጣጣሙ መሆናቸውን ያረጋግጣል፤
- በተለያዩ የሥነ ሕዝብና ልማት ዘርፎች ትግባራ ላይ የተሰማሩትን ድርጅቶች(መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ) እንደ አስፈላጊነቱ ልዩ ልዩ ግብረ-ኃይሎችንና የቴክኒክ ኮሚቴዎችን በማቋቋም ያስተባብራል፡፡
1.2 በሥነ-ህዝብና ልማት ዙሪያ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ ተግባር፤
1.3 የሥነሕዝብና ልማት መረጃዎችና የምርምር አጀንዳዎችን ማዘጋጀትና ጥናቶችን ማካሄድ፤
- የክልሉን ዲሞግራፊ ባህሪያት አዝማሚያ የሚያሳዩ መረጃዎችን ይለያል፣ ይገመግማል፣ በጥናት ላይ በመመስረት ለሚቀርበው የስትራቴጂ መነሻ ሀሳብ እነዲቀርብ ይደረጋል፡፡
- ፖሊሲ-ነክ የሆኑ ክልላዊ የምርምር መርሐ ግብሮችን ለማስፋፋት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ትብብር ያደርጋል፣ በመከታተል ድጋፍ ያደርጋል፡፡
- የሥነህዝብና ልማት ምርምር አጀንዳ ለማዘጋጀት ቢጋር ያዘጋጃል፣መረጃዎችን ይተነትናል፣የአጀንዳውን ረቂቅ አዘጋጅቶ ያቀርባል፡፡
- ከሥነሕዝብና ልማት ጋር የተገናኙ የጥናት ሀሳቦችን ያመነጫል፣ጥናቶችን ለማካሄድ ቢጋርና ፕሮፖዛል ያዘጋጃል፣ለኃላፊው ያቀርባል፡፡
- ለጥናት የሚሆኑ ርእሶችን እንደቅደም ተከተላቸው ይለያል፣ለኃላፊው በማቅረብ ያጸድቃል፡፡
- የሥነሕዝብ ጉዳዮችን በሚመለከት በጥናት የተደገፈ የመረጃ ቋት እንዲዘጋጅ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፡፡
- በስነህዝብና ልማት ዙሪያ ጥናት ከሚያካሄዱ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና ከሌሎች ባለደርሻ አካላት ልምድ በመቀመር ያቀርባል፡፡
- በመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመተባበር የማህበረሰብ የንቅናቄ መድረክ (GO-NGO Population partiners forum) በሚገባ እንዲካሄዱ ያደረጋል፡፡
- የሥነ-ህዝብ ክበባት ዋነኛ የሥነ-ህዝብ መልዕክቶች ማስተባበሪያ በመሆናቸው በክልሉ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ክበባትን እንዲደራጁ ያደርጋል፤የሚመሩበትን መመሪያ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ለስራቸው የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን አቅም በፈቀደ እንዲያገኙ ያደርጋል፤በክበባቱ መካከል የውድድር መንፈስ እንዲጎለብት ያደርጋል፡፡
- በማህበረሰቡ ውስጥ የሬዲዮ ሰሚ ቡድን በማደራጀት በየጊዜው በሚተላለፉ የሥነ-ህዝብ መልዕክቶች ዙሪያ ውይይት በማድረግ ግንዛቤያቸውን እንዲያሳድጉ አሰራሮችን ይዘረጋል፤አፈጻጸሙንም ይከታተላል፡፡
- የኃይይማኖት መሪዎች ፎረም (የምክክር መድረክ) በመፍጠር የተለያየ ትምህርትና ሥልጠና እንዲሰጥ ያደርጋል፤ የኃይይማኖት መሪዎች ትምህርቱን ለተከታዮቻቸው ማስተላለፋቸውን ይከታተላል፤ ያረጋግጣል፡፡
- ለማህበረሰብ የንቅናቄ የምክክር መድረኩ የሚቀርቡ ጥናታዊ ጽሁፎችና የመወያያ ሰነዶች እንዲዘጋጁና እንዲቀርቡ ያደርጋል ፣የጋራ መድረኩ የውይይት ጭብጦችም በቃለ ጉባኤ (proceeding)ተዘጋጅተው እንዲሰራጩ ያደርጋል።
- በየት/ቤቶች የሥነ-ህዝብ ክበባት እንዲቋቋሙና የተቋቋሙትም እንዲጠናከሩ ድጋፍና ክትትል ይደረጋል፡፡
1.4 የሥነ-ህዝብና ልማት ስልጠናዎችን ማዘጋጀትና ቅንጅታዊ አሰራር እንዲፈጠር ማድረግ፤
- በስነ-ህዝብና ልማት መረጃ አዘገጃጀትና አጠቃቀም ላይ የሚሰጡ ሥልጠናዎችን ለሴክተር መስሪያ ቤቶችና ለዞኖች የሥልጠና ማንዋል ያዘጋጃል፣ ሥልጠና ይሠጣል፣ ሙያዊ ድጋፍ ያደርጋል፡፡
- የሥነ-ሕዝብና ልማት ጉዳዮችን የሚመለከቱ ዓውደ ጥናቶች እና ሥልጠናዎች ያዘጋጃል፡፡
- የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ኃላፊነታቸውን በሚገባ እንዲወጡ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፡፡
- በቡድኑ ለሚዘጋጀ ውዕቅ ድግብአት ይሰጣል፣ በተዘጋጀው እቅድ ላይ በመመስረት፣ የግሉን ሥራ ያቅዳል፣ ስለአፈጻጸሙ ሪፖርት ያቀርባል፡፡
