ካፋ ዞን ፕላንና ልማት መምሪያ

የካፋ ዞን ፕላንና ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አስማማዉ አደመ ዓለሙ

የካፋ ዞን አጠቃላይ ገጽታ

የካፋ ዞን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ዉስጥ የሚገኝ ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የዓረቢካ ቡና (Coffee arebica) መገኛ በመሆን የሚታወቅና እጅግ ከፍተኛ የሆነ ተፈጥሯዊ እና ታሪካዊ ሃብቶችን የተጎናጸፈ ዉብ እና አረንጓዴ አካባቢ ነዉ፡፡ በዞኑ ያሉ ነባር ብሄሮች ካፋ፣ ጻራ፣ እና ናይ ሲሆኑ ሌሎች በርካታ ብሄሮች ተዋደዉ እና ተከባብረዉ ይኖራሉ፡፡ የዞኑ አስተዳደር ማዕከል እና የክልሉ የአስተዳደርና ፖለቲካ መቀመጫ ቦንጋ ከተማ ስትሆን ፣ ከተማዋ ከመዲናችን አዲስ አበባ በስተደቡብ ምዕራብ በኩል 460 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡

አስተዳደራዊ መዋቅርን በተመለከተ ዞኑ በ12 ወረዳዎችና በ5 የከተማ አስተዳደር መዋቅሮች የተዋቀረ ሲሆን በስሩ 326 የገጠር እና 44 የከተማ ቀበሌዎችን በድምሩ 370 ቀበሌዎችን የያዘ ነዉ፡፡

የካፋ ዞን ከምድር ወገብ በስተ ሰሜን በግምት ከ6000I እስከ 7025I የሰሜን ንፍቀ ክበብ ትይዩ መስመር (60 እስከ 7.40 ሰሜን ላቲቲዩድ ላይ ይገኛል) የዞኑ ጠቅላላ የቆዳ ስፋት 1063682 ሄክታር ሲሆን ከዞኑ አጠቃላይ የቆዳ ስፋት 8% ደጋ፣70% ወይና ደጋ እና 22% ቆላ የአየር ፀባይ አለዉ፡፡ ቆላማ የአየር ንብረት ከ500 እስከ 1300ሜ ከፍታ ፣ ወይናደጋ ከ1300 እስከ 2200ሜ ከፍታ ያለዉ ሲሆን ደጋማ የአየር ንብረት ከ2200 እስከ 3000ሜ ከፍታ አለዉ፡፡

ዞኑ በሰሜንና ሰሜን ምስራቅ ከኦሮሚያ ክልል፣ በምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ከቤንች ሸኮ ዞን፣ በሰሜን ምዕራብ ሸካ ዞን እና በምስራቅ ከኮንታ ዞን ጋር ይዋሰናል፡፡

በማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ባለስልጣን በ1999 ዓ.ም በተደረገዉ የህዝብና ቤት ቆጠራ የህዝብ ዕድገት አማካይ ግምት መሰረት የ2017 ዓ.ም የካፋ ህዝብ ብዛት ትንበያ እንደሚያመለክተዉ 1,489,228 እንደሆነ መረጃዎች የሚያመለክቱ ሲሆን አሁናዊ የህዝብ እድገት ከፍተኛ ከመሆኑ አንጻር የህዝብና ቤት ቆጠራ ቢካሄድ ከሁለት ሚሊዮን በላይ የህዝብ ቁጥር እንዳለ ይገመታል፡፡

ከጤና አንጻር

በዞኑ ያለ አጠቃላይ ሆስፒታል ብዛት 1

በዞኑ ያለ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ብዛት 4

በዞኑ ያሉ ጤና ጣቢያ ብዛት 50

በዞኑ ያሉ  ጤና ኬላ ብዛት 294

የግል ጤና ተቋማት ብዛትን በተመለከተ

መድሃኒት መደብር 91

ዲያግኖስቲክ ላብራቶሪ 1

ላብራቶሪ 19

ፋርማሲ 14 መሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ::

ከትምህርት አንጻር /የትምህርት ተቋማት መረጃ/

በዞኑ ያሉ የመንግስት ት/ቤቶች ብዛት ከ1-8 567 ፣ ከ9-12 62 ት/ቤት

የግል ት/ቤቶች ብዛት ከ1-8 14 ፣ ኬጂ ት/ቤቶች ብዛት 42

በዞኑ ያሉ የቴክኒና ሙያ ተቋማት ብዛት 1 ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ 5 ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጆች ይገኛሉ 1 መምህራን ትምህርት ኮሌጅ እንዲሁም 1 ዩኒቨርሲቲ ይገኛል፡፡

በማዕድን ዘርፍ

በዞኑ የተለያዩ ማዕድናት የሚገኙ ሲሆን ከነዚህም ዉስጥ ዋና ዋናዎቹ የከሰል ድንጋይ (አዲዮ ወረዳ ) ከፍተኛ የሆነ የብረት ማዕድን ክምችት (ጨታ እና ጎባ ወረዳዎች) በስፋት የሚገኝ ሲሆን በቀጣይ ልዩ ትኩረት ቢሰጠዉ የክልላችንን ብሎም የሃገራችንን የብረት ፍላጎት በመሸፈን ከዉጭ የሚገባዉን ፍላጎት ማስቀረት ይችላል፡፡

ከኢኮኖሚ አቅም አንጻር

የዞኑ ኢኮኖሚ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በግብርና ላይ የተመሰረተ ነዉ፡፡ ቡና ዋነኛዉ የገቢና የዉጭ ምንዛሬ ምንጭ ሲሆን፣ ከዚህ በተጨማሪ የስንዴ ኩታገጠም እርሻ፣የቦንጋ በግ፣እንሰት፣በቆሎ፣ጤፍ፣ሰሊጥ፣ማርና የተለያዩ ቅመማ ቅመሞች በስፋት ይመረታሉ፡፡

የቱሪስት መዳረሻዎች

በዞኑ ከሚታወቁ የቱሪዝም መስህቦች መካከል የባርታ ፏፏቴ፣ኤልኤሎ ፏፏቴ፣ ጉርጉቶ(የተፈጥሮ የእግዜር ድልድይ) የእናት ቡና የሚገኝበት ማንኪራ ቡኒ መንደር፣ዳዲበን ፍል ዉሃ ፣ጥንታዊና ታሪካዊ አብያተ ክርስቲያናትና የቶንጎላ መስጊድ፣ የካፋ ነገስታት መካነ መቃብር፣ የማሽቃሮ በዓል አከባበር፣ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የተመዘገበ ታዋቂ የባዮስፌር ጥበቃ ቀጠና (Kafa Biosphere Reserve) ከ760‚000 ሄክታር በላይ መሬት የሚሸፍን ጥቅጥቅ ያለ የተፈጥሮ ደንና በዉስጡ ከ300 በላይ የአእዋፍ ዝርያዎች እና ሌሎች ዋና ዋና የቱሪዝም መዳረሻዎች ናቸዉ፡፡