Background Of West Omo Zone
Location and Area
ምዕራብ ኦሞ ዞን በደ/ምዕራብ ኢትዮጲያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት
ከሚገኙ ዞኖች በሚያዝያ 23/2011 ዓ.ም በአድስ መልክ
መመስረቱ ይታወቃል፡፡ ዞኑ በሀገሪቱ በደቡብ
ምዕራብ አቅጣጫ ከአዲስ አበባ 671 ኪ/ሜትርና ከክልሉ
ርዕሰ ከተማ ቦንጋ 200 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ይገኛል። ዞኑ
በሰሜንና በሰሜን ምስራቅ ከከፋ ዞን፣ በሰሜን ምዕራብ ከቤንች ሸኮ ዞን፣ በደቡብ ምሥራቅ ከደቡብ ኦሞ ዞን፣ በደቡብ ምዕራብ
ከጋምቤላ ክልልና በደቡብ ከደቡብ ሱዳን ሪፖብሊክ ጋር ይዋሰናል። ዞኑ 3 ክፍለ ከተማዎችና በ7 ወረዳዎች በ114 ቀበሌ አስተዳደር የተከፋፈለ ሲሆን የቆዳ ስፋቱ 1,458,400 ሄ/ር እንደሚሆንና በ1ስኩዌር
ኪሎ ሜትር በአማካይ 20.6 ህዝብ እንደሚኖር ይገመታል። ዞኑ
የሚገኝበት በስተምስራቅ
/Latitude/ 6.6384755 እና በስተ ምዕራብ
/Longitude/ 35.7817109 ይገኛል፡፡ Population size and distribution የ1999
ዓ.ም የህዝብና
ቤቶች ቆጠራ ውጤትን መሰረት በማድረግና በዞኑ ካሉ ወረዳዎች የህዝብ ቁጥር መረጃ በመሰብሰብ በተገኘው መረጃ በ2017 ዓ.ም የዞኑ ህዝብ
ብዛት ወ 163,542 ሴ 174,236 ድ 337,778 በዞን ማዕከል ፣ በከተማ አስተዳደርና በ7ቱ ወረዳዎች የሚገኙ
አራቱ /4/ ነባር ብሄረሰቦች ማለትም
የመኤኒት፣የዲዚ፣የሱርማና ዚልማሞ ብሔረሰቦችንና በሰፈራ ጣቢያዎች ተካቶ ያሉ የአማራ፤ የከምባታና የሲዳማ ብሔረሰቦችን ያካተተና
በተጨማሪም በዞኑ ዉስጥ ባሉ ወረዳ ከተማዎች በንግድና በመንግስታዊ ስራ የተሰማሩ ሌሎች ኢትዮጵያዊ ብሔረሰቦች ይገኛሉ፡፡ በዞኑ ዉስጥ በዋናነት የመኤኒት፣ የዲዚ፣የሱርማና የዚልማሞ
ብሔረሰቦች የሚኖሩ ሲሆን ከነባሩ ህዝብ ጋር በኢትዮጵያ ዉስጥ የሚገኙ ሌሎች ብሄር ብሔረሰቦች በአንድነት ተሳስበዉና ተፈቃቅደዉ
ተከባብረዉ የሚኖሩበት ዞን ነዉ ፡፡ አብዛኛዉ ህዝብ የሚተዳደረዉ በከፊል አርብቶ አደርነት፤ በግብርና እና በማዕድን ምርት
የሚተዳደር ህዝብን ጨምሮ የያዘ ነዉ፡፡ የህዝብ አሰፋፈሩ በመኖሪያ አካባቢ በገጠር 294,179 (87.09%) እና በከተማ 43,599 (12.91%) ህዝብ እንደሚኖሩ ይገመታል። Air condition የዞኑ መልከዓ ምድራዊ አቀማመጥ ከባህር ጠለል በላይ ከ250 - 3000 ሜትር ውስጥ የሚገኝ በመሆኑ የአየር ፀባዩ ለተለያዩ
የግብርና ሥራዎች ምቹ ነው። አመታዊ አማካይ የዝናብ መጠኑ ከ400-2000
ሚ/ሜ ነው ። አማካይ የሙቀት መጠን 15.1oc-27.5oc ይደርሳል ።
ከስነ-ምህዳር ስብጥር አንፃር ቆላማ
52%፣ወይና ደጋ 43% እና ቀሪው 5% ደጋ የአየር ፀባይ አለው ። ዞኑ በተለይ በሀገሪቱ
የውጭ ምንዛሪ ከፍተኛ ድርሻ ያለው የቡና፤የቅመማ ቅመም፤ሩዝና
ሰሊጥ ምርት፤የተለያዩ የዕምቅ ሀብት ባለቤት ሲሆን ለአብነት ሊጠቀሱ የሚችሉ የኮንስትራክሽን ማዕድናት፣ ወርቅ፤ ዕብነ በረድ
ሌሎች የተለያዩ የከበሩ ማዕድናት፣የተለያዩ ዓይነት ያላቸው እጽዋትና እንስሳት የሚገኙበት ዞን ሲሆን በክልሉ ከሚገኙ ብሔራዊ
ፓርኮች ውስጥ የኦሞ ብሔራዊ ፓርክ በዚሁ ዞን ይገኛል።
በዚህ ፓርኩ ውስጥ ጎሽ፤ ዝሆን፤ ቀጭኔ፤ ዲፈርሳ፤ ቆርኪ፤ እና
በኢትዩጵያ ብቸኛና ብርቅዬ የሆነችው ውድንቢ/ኢላንድ/ ጨምሮ ከ70 በላይ አጥቢ እንስሳት፤ ከ3መቶ በላይ አዕዋፍ እና ተሳቢ
እንስሳት ያቀፈ ፓርክ ነው Education ከማህበራዊ አገልግሎት ሽፋን አንፃር ከትምህርትና ከጤና አገልግሎት አኳያ በ2017 የትምህርት ዘመን 192 1ኛ
ደረጃ 1-8ኛ ት/ቤቶች፣ 14 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች እና 1 የግል ት/ቤት ይገኛሉ። 1ኛ ደረጃ 1-8ኛ 58,899 ተማሪዎች፣ 2ኛ ደረጃ /ከ9 —12ኛ/ 5,086 ተማሪዎች እና የግል ት/ት ቤት /ኬጅ/ 235 ተማሪዎች እንዲሁም በመንግስት ት/ትቤት 0 ክፍል 26,071 ተማሪዎች ይገኛሉ ፡፡ እንዲሁም በዞኑ ሁለት /2/ ፖሊ ቴክኒክ የሙያ ኮሌጅ በክልል መንግስት ተገንብተዉ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ የትምህርት ንጥር ተሳተፎ አጠቃላይ በዞኑ 59.15 % ደርሷል ፡፡ Water cevorege የውሃ ሽፋን በተመለከተ በዞኑ በገጠር 19.79%
ደርሷል ። ከመሠረተ ልማት አንፃር በዞኑ ካሉት 7 ወረዳዎች ሙሉ ክረምት እና ከበጋ የትራንስፖርት አገልግሎት ሊያሰጥ የሚችል መንገድ
ያላቸው ወረዳዎች 5 ሲሆኑ እነዚህም ሚ/ ጎልዲያ፤ጎሪ-ጌሻ፣ ሚ/ ሻሻ፣ ቤሮ እና ማጂ
ሲሆኑ ቀሪዎቹ 2 ወረዳዎች ማለትም ሱሪ እና ጋችት
ወረዳዎች ለህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት የማያሰጥ መንገድ ምቹ ባለመሆኑ ማህበረሰቡ የትራንስፖሪት ስምሪት አገልግሎት ማግኘት እየቻሉ እንዳልሆነ
መረጃው ያሳያል፡፡ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ መብራት የሚያገኙ ወረዳዎች 4 ሲሆኑ እነዚህም ሜ/ ጎልዲያ፣ ቤሮ፣ ሜ/ሻሻና ጋችት ብቻ ሲሆኑ የማጂ፣ጎሪ ጌሻ፤ እና ሱሪ ወረዳዎች የመብራት አገልግሎት
ማግኘት ያልጀመሩ ናቸዉ፡፡ Health በ2016 በዞኑ ያሉ የጤና ተቋማት 2 ሆስፒታል፣ 99 ጤና ኬላ እና 16 ጤና ጣቢያ በጥቅሉ 117 ተቋማት ይገኛሉ፡፡ 322 የጤና እክስቴሽን
ባለሙያ፣ 378 ዲፕሎማ ባለሙያ፣ 193 ድግሪ እና
11 MPH/MSC በአጠቃላይ 904 ባለሙያዎች ይገኛሉ ፡፡ Agricultural & Natural Resource የዞኑ
ኢኮኖሚ አንቅስቃሴ ሲቃኝ 90% ያህሉ የዞኑ ህዝብ የሚተዳደረው
በአርብቶ አደር እና በከፊል አርብቶ አደርነት እንዲሁም በንብ ማነብ ሲሆን ይህም አብዛኛው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የተመሠረተው
እንስሳት እርባታ መሆኑን ያሳያል። በዚሁ በተጠቀሰው ዘርፍ
በ2016 ዓ/ም በዞኑ 2‚482,439 የቀንድ ከብቶች፣ 958,903 ፍየሎች፣ 1‚178,134
ዶሮዎች፣ 6,189 በቅሎዎች፣ 39,154 አህዮች፣918,205 በጎችና 46,331 ፈረሶች
ይገኛሉ። የምዕራብ ኦሞ ዞን አጠቃላይ የቆዳ ስፋት 1,458,400
ሄክታር ሽፋን ሲኖረዉ ከዚህ ዉስጥ የለማ 385,880
/26.46%/ ሄክታር መሆኑን በ2016 በጀት ዘመን
የተጠናከረዉ መረጃ ያመለክታል፡፡
የምህራብ ኦሞ ዞን ፕላንና ልማት መምሪያ በዞኑ ከሚገኙ መምሪዎች አንዱ ሲሆን በሰባት(7) የወረዳ ፕላንና ልማት ጽ/ቤቶች የተዋቀረና በሶስት(3) የከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ጽ/ቤቶች የተዋቀረ ሲሆን በዞኑ በድምሩ አስር(10) መዋቅሮች ሲኖሩት የፕላን ልማት ጽ/ቤት የተዋቀረባቸው በሰባቱ(7) ወረዳዎች ሲሆን የከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ጽ/ቤቶች መዋቅር ሲስተካከል እንደሚዋቀሩ ያለዉ መረጃ ያመላክታል፡፡