የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሲመሰረት የክልሉን አስፈፃሚ መ/ቤቶች ሲቋቋሙ የፋይናንስና ፕላን ቢሮ በጥምረት ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በሚል ሲያሜ በቢሮነት ተቋቁሞ ከህዳር 2014 እስከ 2016 በጀት ዓመት መጠናቀቂያ ድረስ በፋይናንስ ስር የቆየ ሲሆን በተሻለ አፈጻጸም እና የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት ታስቦ ለ2017 በጀት ዓመት እንደገና በአዋጅ ቁጥር 33/2016 ፕላን በቢሮ ደረጃ ተሻሽሎ ተቋቁሟል፡፡ ቢሮው የክልሉን አጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታዎችን በማጥናት ማነቆ የሆኑ ችግሮችን በመለየት የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ማመላከትና የክልሉን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና መልካምድራዊ መረጃዎች ጥራቱን በጠበቀና በአስተማማኝ ሁኔታ በማዘጋጀት ለውሳኔ ሰጪ አካላት፣ ለፖሊሲ አውጪዎች፣ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና እንዲሁም ለጥናትና ምርምር ተቋማት ያቀርባል፡፡
በክልሉ ተግባራዊ የሚደረጉ የካፒታል ፕሮጀክቶች የተጣለባቸውን ግቦች በማሳካት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችል ጠንካራ የክትትልና ግምገማ ስራዎችን ተግባራዊ ማድረግ፣ የክልሉ የህዝብ እድገት ምጣኔ ከክልሉ ኢኮኖሚ የዕድገት ምጣኔ ጋር እንዲጣጣም ማድረግና በሥነ ህዝብና ልማት ዙሪያ ለማህበረሰቡ ሰፊ የትምህርትና ቅስቀሳ ስራዎችን መተግበርና በክልሉ የሚገኘው የተፈጥሮ ሀብትን በአግባቡ በመጠቀም ታዳሽ በሆኑ የተፈጥሮ ሀብት ላይ በማተኮርና ታዳሽ ያልሆኑ ሀብቶችን ቀጣይ ትውልድን ታሳቢ በማድረግ በተመጣጣኝ መልኩ ጥቅም ላይ እንዲውሉ በማድረግ የክልሉ ኢኮኖሚ ዕድገት ቀጣይነትና ዘላቂነት እንዲኖረው ማረጋገጥ በመሠረታዊ ተልዕኮዎች ውስጥ የተካተቱ ናቸው፡፡በተጨማሪም በክልሉ የተገኘውን ሀብት በዕቅድ በመምራትና አፈጻጸሙን በመከታተልና በመገምገም፣ የልማት ዕቅድና ፖሊሲ አፈፃጸም ጥናትና ትንተና ያካሂዳል፡፡የፕላን ቢሮ ከክልል እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ በአዲስ መልክ እንዲደራጅ ተደርጎ መዋቅር ተቀርጾለታል፡
በክልል ደረጃ የቢሮ ኃላፊ እና 2 ምክትል ቢሮኃላፊዎችና ዘርፎች 10 ዳይሬክቶሬቶችእና በ50 ባለሙያዎችየተደራጀሲሆንበሁሉምዞኖች፣ወረዳዎችናከተማአስተዳደሮችበመምሪያእናበጽ/ቤትደረጃመዋቅርተቀርጾለትተግባራዊበመደረግላይይገኛል፡፡የፕላንቢሮከክልልእስከታችኛውመዋቅርድረስበአዲስመልክእንዲደራጅተደርጎመዋቅርተቀርጾለታል፡፡
በማኀበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ጥናቶችን በማካሄድና የፖሊሲ ማሻሻያ ሀሳቦችን በማመንጨት፣ ግልፀኝነትና ተጠያቂነት በሰፈነበት አሰራር ዘመናዊ የልማት ዕቅድና መረጃ፣ በመዘርጋት፣የልማት አጋሮችን በማስተባበርና የሕዝብ ቁጥር ዕድገት ከኢኮኖሚ እድገት ጋር እንዲጣጣም በመስራት በክልሉ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማት እንዲረጋገጥ ማስቻል፡፡
የተደራጀ መረጃ መሰብሰብ. የተደራጀዉን መረጃ ወደ ዳታ ቤዝ ማስገበትና ለጥቅም እንዲዉል ማስቻል፡፡. ለቀጣይ ዕቅድ ግብዓት የሚሆኑ መረጃወቸን ማደራጀት.