መግቢያ
ሙስናና ብልሹ አሰራር የሀገራችንንም ሆነ የክልላችንን ሁሉ አቀፍ ብልጽግና የሚገታ እና ጥረታችንን የሚያደናቅፍ ተግባር መሆኑን በመገንዘብ የክልሉ መንግስት የፀረ ሙስና ኮሚሽን በአዋጅ ቁጥር 17/2015 ዓ.ም በማቋቋም በአዲስ መልክ ስራውን ጀምረዋል፡፡
በመሆኑም በክልል ቢሮዎች የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እንዲመደብ በተፈቀደዉ መሠረት ፐላን ልማት ቢሮም መልካም ዕሴቶችና መልካም ሥነ- ምግባር በመገንባት የሙስና ወንጀል ምንነት፣አደጋው እና መታገያ መንገዶች ዙሪያ የግንዛቤ ትምህርት በመስጠት ሙስናና ብልሹ አሠራር ከመፈጠሩ በፊት አስቀድሞ በመከላከል እንድሁም ሙስና ተፈፅሞ ሲገኝ ፈጥኖ ማረምና ማስተካከል ይሆናል፡፡
1. ተልዕኮ
ሙስናና ብልሹ አሠራር ለመከላከል የሚያስችል የሥነ ምግባር አስተምህሮዎችን በማስተማር፣በጥናት ላይ የተመሠረተ የቅድመ ሙስና መከላከል ሥራዎችን በመሥራት፣ በህጉ መሠረት የሀብት ማሳወቅና ማስመዝገብ ሥራዎችን በብቃት በመፈፀም እና ከሌሎች የባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመሥራት ውጤታማነትን ማረጋገጥ፡፡
2. ራዕይ
በ2022 ሙስናና ብልሹ አሰራር የተቋሙ የመልካም አስተዳደር፣ የልማትና ፍትሃዊ የሀብት አጠቃቀም እንቅፋት እንዳይሆን በማድረግ በክልሉ ካሉት ቢሮዎችና ተቋማት ግንባር ቀደም ተቋም ሆኖ ማየት
3. የእሴቶች
ማጠቃለያ
የደ/ ምዕ/ ኢ/ ህ/ ክ/ መን/ ፕላን ልማት ቢሮ በሥነ- ምግባርና ፀረ – ሙስና ዙሪያ ዉጤት ለማስመዝገብ ትኩረት አድርጎ ለመሥራትና ቢሮዉ ተልዕኮዉን መሸከም የሚያስችል ተቋማዊ አደረጃጀቱን በማጠናከር የደ/ ምዕ/ ኢ/ ህ/ ክ/ ምክር ቤት አስፈጻሚ መ/ቤቶችን በተጨማሪ ለማሻሻልና ለማቋቋም በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 33 / 2016 መሰረት ፕላንና ልማት ቢሮ የተሰጠዉን ተግባርና ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስችል ቁመና በመፍጠር እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት የቢሮዉ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙሰና ክፍልም በተቋሙ የጥቆማ መቀበያ ስርዓት በመዘርጋት ፤ የአስቸኳይ ሙስና የመከላከል ሥርዓት በመዘርጋት ፤ የመንግስት ሀብተና ንብረት የማዳንና የቢሮዉን ዋና ዋና ሥራዎች ለህዝብ ተደራሽ የማድረግ እንዲሁም የቢሮዉን ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎችን መነሻ በማድረግ ለስነ – ምግባርና ፀረ – ሙስና የተለዩ በግቦቹ ሥር የተቀመጡ ዋና ዋና ተግባራትን በመዉሰድ ብሎም መልካም አጋጣሚዎችንና ስጋቶችን በመለየት የመብቴሄ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥና ጠንካራ የክትትልና ድጋፍ ሥርዓትን መሥራት፡፡