የስታስቲክስና ጂኦ-ስፓሻል ዳታ ስርዓት አስተዳደርና ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት

አቶ አምሳሉ ዳምጤ ከበደ

የስታስቲክስና ጂኦ-ስፓሻል ዳታ ስርዓት አስተዳደርና ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት

የስታስቲክስና ጂኦ-ስፓሻል ዳታ ስርዓት አስተዳደርና ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬትኃላፊነትና ተግባር

  • በክልሉ የተቀናጀ የመረጃ አያያዝና አጠቃቀም ስርዓት በመዘርጋት ወቅታዊ፣ ፈጣንና ጥራት ያለውን መረጃ ተደራሽነትን በማስፋፋት የክልሉን ዕድገት ማፋጠን፣
  • ዘመናዊ የመረጃ፣ አያያዝና አስተዳደር ስርዓትን በማጠናከር፣ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ ላይ የተመሠረተ ጥናት በማካሄድ፣ትክክለኛ ውሣኔ እንዲወሰን ያደረጋል፡፡
  • በየአስተዳደር እርከኑ ላሉ የመረጃ አመንጪ ሴክተር መ/ቤቶች የሥልጠና ፍላጎት ዳሰሳ ጥናትን በመተንተን የስልጠናና የአቅም ግንባታ አገልግሎቶች ይሰጣል፣ እንዲሰጥ ያደርጋል፣
  • ዓመታዊ ስታቲስቲካዊ አብስትራክት ዶክመንት በልዩ ልዩ ርዕሶች ያዘጋጃል፣
  • አጠቃላይ ክልላዊ አትላስ ካርታ ዶክመንት ማዘጋጀት፣
  • በስታቲስቲካዊና ተያያዥ ስራዎች ላይ በሚቀርብ የቀጥታ ድጋፍ ጥያቄ መሰረት ሙያዊ ድጋፍ ያደርጋል፣
  • ክልላዊ የስታቲስቲክስ ስርዓቱን በተሻለ መንገድ ለመምራት የሚያግዙና የተለያዩ የልምድ ልውውጥ፣ የምክክር መድረኮችና ዉይይቶች ያከናውናል፣
  • የመረጃ ጥራት መመዘን በሚመለከት ተገቢዉን መግለጫ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣
  • ለአቅም ግንባታ ስራዎች የሚውሉየስታትስቲካል መረጃ ልዉዉጥ አጠቃቀምና ዳታ-ቤዝ አስተዳደር ደንብ፣ መመሪያና ማኑዋል እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ ይገመግማል፣ ያበለጽጋል፣ የአቅም ግንባታ ስልጠና ይሰጣል፣
  • የአቅም ክፍተቶችን በመለየት አስፈላጊዉን የስራ ላይ ስልጠና (On Job Training) እንዲያገኙና የተሰጣቸዉን ኃላፊነት በብቃት እንዲወጡ አቅማቸውን ለመገንባት የሚያስችል የቴክኒክና የአቅም ግንባታ ስልጠና ይሰጣል፣
  • ከዞንና በክልል ማዕከል የሚገኙ የሴክተር መስሪያ ቤቶች የሚሰበስቡ ስታቲስትካል መረጃ የጥራት ደረጃ የሚገመገምበትን ስርዓት ይዘረጋል፣
  • Regional data center ከሁሉም መንግስት ተቋማት (ከክልል እስከ ወረዳ መዋቅር) የተቀናጀ እንዲሆን ማስቻል፣
  • የሁሉም ሴክተር ስታቲስቲካል እንዲኬተር (Statistical Indicator) በተሟላ መንገድ እንዲዘጋጁ ይደረጋል፡፡
  • የክልሉ መሠረታዊ ስታስቲካል መረጃዎች በቀላሉ ተደራሽ እንዲሆን online system ማልማት እና መረጃው በጊዜው update እንዲሆን የተጠናከረ ሥራ መስራት እና ክትትል ማድረግ፣
  • ከዞንና በክልል ማዕከል የሚገኙ የሴክተር መስሪያ ቤቶች የሚሰበስቡ ስታቲስትካል መረጃ የጥራት ደረጃ በተለያዩ የመተንተኛ ሶፍትዌሮችን /IMIS/REDATAM/,GIS,STATA,SPSS, በመጠቀም በመተንተን፣ በስታቲስቲካዊ ሰንጠረዦችን፣ ግራፎችን፣ ቻርቶችን መተንተናቸውን ትክክለኛነቱን ያረጋግጣል፣
  • በየደረጃዉ ባሉ አስተዳደራዊ መዋቅር የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ መልክዓ-ምድራዊና ስታትስቲክስ መረጃ ልዉዉጥ ሥርዓት ወጥ የሚሆንበትን የአሰራር ሥርዓት ይዘረጋል፣
  • የስታትስቲካዊ መረጃ የደረጃ ምደባ፣ የጥራት ቁጥጥርና ከዘርፉ ጋር ተያያዥነት ባላቸው የተሻለ አፈጻጸም ከተለያዩ ምንጮች ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመርና ከክልሉ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማጣጣም ጥቅም ላይ እንዲዉሉ ተደራሽ ያደርጋል፡፡
  • በክልል አቀፍ ደረጃ ለሚከናወኑ የናሙና ጥናቶች አግባብ ካላቸዉ ከሌሎች የስራ ሂደቶች ጋር ግንኙነት በመፍጠር የሚከናወኑ ጥናቶችና ቆጠራዎች ከተቀመጡ የስታቲስቲክስ ደረጃዎች አኳያ የጥራት ደረጃቸዉን እንዲጠብቁ ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፣
  • የክልሉን ስታቲስቲክስ ጥራት ስርዓቱን የሚያቀላጥፉ አዳዲስ አሰራሮችና ቴክኖሎጂዎች ላይ የዕዉቀትና የክህሎት ሽግግር ግንባታ ሂደቱን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ያረጋግጣል፣
  • ክልላዊ ስታትስቲካል መረጃ ማረጋገጫ አገልግሎት አሰጣጥ በመዘርጋት (Authentication of official Statistics of the Region) የመረጃ ቁጥጥር በማረጋገጥ አገልግሎትን በመጨመር ክልላዊ ስታቲስቲካል መረጃ ቁጥጥር ስርዓት መዘርጋት፣
  • የመረጃን ጥራት ለመጠበቅ እንዲቻል የተዘጋጁት የተለያዩ የመረጃ ጥራት ማስጠበቂያ ዘዴዎችን በሁሉም መረጃ አመንጪ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የመረጃ አያያዝ ስርዓታቸውን ይገመግማል፣ ጠንካራና ደካማ ጎናቸውን በማመልከት የጥራት ማረጋገጫ ይሰጣል፣