በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግሥት ፕላንና ልማት ቢሮ መዋቅር
የቢሮ ኃላፊ
የልማት መረጃ ሥርዓት አስተዳደርና ስነ-ሕዝብ ልማት ጉዳዮች ዘርፍ
- የስታስቲክስና ጂኦ-ስፓሻል ዳታ ስርዓት አስተዳደርና ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት
- የስነ ሕዝብ ልማት ትምህርትና ቅስቀሳ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
- ካርቶ ግራፊና ጂ-አይ-ኤስ ዳይሬክቶሬት
የማክሮ ኢኮኖሚ ዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዘርፍ
- የልማት ፕሮጀክቶች ዳይሬክቶሬት
- የመሪ ፕላን ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት
- የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማኔጅመንት ጥናትና ትንተና ዳይሬክቶሬት
አሰተዳደር ዘርፍ
- የሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ዳይሬክቶሬት
- የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
- የልማት እቅድ በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት
- የኢንስፔክሽንና ውስጥ ኦዲት ድጋፍና ክትትል ዳይሬክቶሬት
- የኢንስፔክሽንና ውስጥ ኦዲት ድጋፍና ክትትል ዳይሬክቶሬት
- የህዝብ ግንኙነት
- የህዝብ ግንኙነት
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጲያ ሕዝቦች ክልል መንግሥት ፕላንና ልማት ቢሮ መዋቅር
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሲመሰረት የክልሉን አስፈፃሚ መ/ቤቶች ሲቋቋሙ የፋይናንስና ፕላን ቢሮ በጥምረት ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በሚል ሲያሜ በቢሮነት ተቋቁሞ ከህዳር 2014 እስከ 2016 በጀት ዓመት መጠናቀቂያ ድረስ በፋይናንስ ስር የቆየ ሲሆን በተሻለ አፈጻጸም እና የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት ታስቦ ለ2017 በጀት ዓመት እንደገና በአዋጅ ቁጥር 33/2016 ፕላን በቢሮ ደረጃ ተሻሽሎ ተቋቁሟል፡፡ ቢሮው የክልሉን አጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታዎችን በማጥናት ማነቆ የሆኑ ችግሮችን በመለየት የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ማመላከትና የክልሉን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና መልካምድራዊ መረጃዎች ጥራቱን በጠበቀና በአስተማማኝ ሁኔታ በማዘጋጀት ለውሳኔ ሰጪ አካላት፣ ለፖሊሲ አውጪዎች፣ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና እንዲሁም ለጥናትና ምርምር ተቋማት ያቀርባል፡፡
በክልሉ ተግባራዊ የሚደረጉ የካፒታል ፕሮጀክቶች የተጣለባቸውን ግቦች በማሳካት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችል ጠንካራ የክትትልና ግምገማ ስራዎችን ተግባራዊ ማድረግ፣ የክልሉ የህዝብ እድገት ምጣኔ ከክልሉ ኢኮኖሚ የዕድገት ምጣኔ ጋር እንዲጣጣም ማድረግና በሥነ ህዝብና ልማት ዙሪያ ለማህበረሰቡ ሰፊ የትምህርትና ቅስቀሳ ስራዎችን መተግበርና በክልሉ የሚገኘው የተፈጥሮ ሀብትን በአግባቡ በመጠቀም ታዳሽ በሆኑ የተፈጥሮ ሀብት ላይ በማተኮርና ታዳሽ ያልሆኑ ሀብቶችን ቀጣይ ትውልድን ታሳቢ በማድረግ በተመጣጣኝ መልኩ ጥቅም ላይ እንዲውሉ በማድረግ የክልሉ ኢኮኖሚ ዕድገት ቀጣይነትና ዘላቂነት እንዲኖረው ማረጋገጥ በመሠረታዊ ተልዕኮዎች ውስጥ የተካተቱ ናቸው፡፡በተጨማሪም በክልሉ የተገኘውን ሀብት በዕቅድ በመምራትና አፈጻጸሙን በመከታተልና በመገምገም፣ የልማት ዕቅድና ፖሊሲ አፈፃጸም ጥናትና ትንተና ያካሂዳል፡፡
የፕላንና ልማት ቢሮ በክልል ደረጃ የቢሮ ኃላፊ እና 2 ምክትል ቢሮ ኃላፊዎችና ዘርፎች 10 ዳይሬክቶሬቶች እና በ50 ባለሙያዎች የተደራጀ ሲሆን በሁሉም ዞኖች፣ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች በመምሪያ እና በጽ/ቤት ደረጃ መዋቅር ተቀርጾለት ተግባራዊ በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡
ተልዕኮ
በማኀበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ጥናቶችን በማካሄድና የፖሊሲ ማሻሻያ ሀሳቦችን በማመንጨት፣ ግልፀኝነትና ተጠያቂነት በሰፈነበት አሰራር ዘመናዊ የልማት ዕቅድና መረጃ፣ በመዘርጋት፣ የልማት አጋሮችን በማስተባበርና የሕዝብ ቁጥር ዕድገት ከኢኮኖሚ እድገት ጋር እንዲጣጣም በመስራት በክልሉ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማት እንዲረጋገጥ ማስቻል፡፡
ራዕይ
ኢኮኖሚያዊና ማኀበራዊ ዕድገትን በማስፈን የክልሉ ሕዝብ ከድህነት ተላቆ “ኢትዮጵያ አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት” ሀገራዊ ራዕይ በ2024 ዓ/ም ተሳክቶ ማየት፡፡
የፕላንና ልማት ቢሮ ተግባርና ኃላፊነት
የክልሉ ፕላን ቢሮ የደቡብ ምዕራብ ኢት/ያ ክልል ምክር ቤት አስፈፃሚ መ/ቤቶችን በተጨማሪ ለማሻሻልና ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 33/2016 ተቋቁሟል፡፡ በዚህ አዋጅ መሠረት የክልሉ ፕላን ቢሮ ቀጥሎ የተመለከቱት አበይት ተግባርና ሀላፊነት የመፈጸም ስልጣንና ኃላፊነት ተሰጥቷል፡፡
- የክልሉን የረጅም፤ የመካከለኛና የአጭር ጊዜ ዕቅድ ያዘጋጃል፤ አፈጻጸማቸውን ይከታተላል፤ ይገመግማል፤ ሪፖርት በማዘጋጀት ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፤
- የክልሉን መንግሥት የካፒታል ፕሮጀክቶች የአዋጭነት ጥናት ያካሂዳል፤ ይገመግማል ያስፀድቃል፤
- የክልሉን የካፒታል ፕሮጀክቶችን አፈፃፀም ክትትልና ግምገማ ያደርጋል፤ ወቅታዊ ሪፖርት በማዘጋጀት አግባብነት ላላቸው አካላት ያቀርባል፤
- የክልሉን ዓመታዊ የሀብት ግመታ ሰነድ/RGDP/ ያዘጋጃል ለክልሉ መስተዳድር ም/ቤት በማቅረብ ያፀድቃል፤
- የክልሉን የኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና መልከዓ ምድራዊ መረጃዎችን ማሰባሰብ፣ ማደራጀት፣ ትንተና በማድረግ ለተጠቃሚዎች ማሰራጨት፡፡
- የክልሉን ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ልማት ስርጭትና የመልከዓ ምድራዊ ገጽታን የሚያሳይ አትላስ ካርታ ማዘጋጀት፣
- የክልሉ መንግስት መ/ቤቶች በስራ ኃላፊነት የሚያመነጩትን ስታትስቲካዊ መረጃዎችን የማሰባሰብ የማደራጀት የመተንተንና ለተጠቃሚዎች ተደራሽ እንዲሆን የማድረግ እንዲሁም ስታንዳፍዱንና ጥራቱን ጠብቆ እንዲዘጋጅ ድጋፍ፣ ክትትልና ኦዲት ያደርጋል በኦዲት ግኝት መሰረት ተገቢውን የማስተካከያ እርምጃ መውሰድ፣
- የክልሉን የመረጃ ክፍተት ለማሟላት የጥናት ምርምር ስራዎችን ማከናወን፣
- የክልሉን የስታትስቲክስ መረጃ ስርዓት በማዘመን ለመንግሰታዊ መስሪያ ቤቶች ድጋፍ ይሰጣል፣ ስራውን በማስተባበር መምራት፣
- የሥነ ህዝብ ጉዳዮችን በልማት እቅድ አካቶ ከመተግበር አኳያ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ማስተባበር፣
- በስነ ህዝብ ጉዳዮች የማህበረሰቡንና የአመራር አካላትን ግንዛቤ ለማጎልበት የሚያስችሉ የትምህርት ቅስቀሳ ስራዎችን ማካሄድ፣
- የሥነ ህዝብና የልማት ጉዳዮቸን በተመለከተ የጥናትና ምርምር ተግባራትን ማከናወን
- በየአስተዳደር እርከን የሚገኙ የስነህዝብ ም/ቤቶችን በማጠናከርና ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር የ5 አመት የስነ ህዝብ ፕሮግራም ያዘጋጃል፡ ለስነ ህዝብ ም/ቤት ማቅረብ ያስጸድቃል ተግባራዊነቱን መከታተል፣ መገምገም አቅጣጫ ማስቀመጥ፣