የሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ዳይሬክቶሬት

photo_2026-02-27_09-44-34

አቶ ሽመልስ ካሌብ ናፋ

የሰዉ ሀብት አስተዳደር ዳይሬክተር


የሰው ሀብት ሥራ አመራር  ዳይሬክተር ዋና ዋና ተግባራት

  • የዳይሬክቶሬቱን ተግባራት ያቅዳል፣ ያደረጃል፣ ይመራል፣ይከታተላል፣ ይደግፋል፣ ይወስናል ይቆጣጠራል፣ የስራ አፈጻጸም ይገመግማል፣  ክፍተቶችን ይለያል፣ ያበቃል፣
  • ከዘርፉ ስትራቴጂክ ዕቅድ የተመነዘረ ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣
·       የቢሯችን ሠራተኞች ጡረታ መለያ ቁጥር ማዉጣት ፣ ሠራተኞች  በሥራ ገበታቸው ላይ ዕለት በዕለት መገኘታቸው ቁጥጥርና ክትትል ማድረግ ፣  የሥራ ልምድ፣ የዋስትና ድጋፍና  የአገልግሎት ማቋረጥ ደብዳቤ አዘጋጅቶ መሰጠት
  • ለተቋም ሠራተኞች መንግሥት በወጣው የምዘና ስርዓት መሠረት በየወቅቱ እንዲመዘኑ ያደርጋል፣ በምዘናው ውጤት መሠረትም ቀጣይ ተግባራትን ያካናውናል፣
  • በተቋሙ የበላይ ኃላፊዎች በሚሰጠው የሥልጣን ውክልና መሠረት በሰው ሃብት ሥራ አመራርና አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጣል፣ ወይም የሚሰጡ ውሳኔዎችን ተግባራዊነት ይከታተላል፣
  • በመንግሥት ሠራተኞች መመሪያዎችና ደንቦች መሠረት ለተቋም የቅጥር፣ የደረጃ ዕድገት፣ ዝውውር፣ የድስፕሊን፣ የቅሬታ ማስተናገጃና እንዲሁም ሌሎች አግባብነት ያላቸው  ኮሚቴዎች እንዲቋቋሙና ተግባራዊ እንዲሆኑ ይከታተላል፣
  • አዲስ ለሚቀጠሩ ሠራተኞች ስለ መንግሥት መመሪያዎችና ደንቦች እንዲሁም ተቋሙ ስለተቋቋመበትና ስለሚጠበቅበት ውጤት እንዲሁም ስለ መሥሪያ ቤቱ ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች ኃላፊነት የማስተዋወቂያ ስልጠና (`Inducation) እንዲሰጥ በማድረግ ወደ ሥራ እንዲሰማሩ ያደርጋል፣
  • የዳይሬክቶሬቱን  ወቅታዊ የሥራ አፈጻጸም ለበላይ አካል ሪፖርት ያቀርባል፣
  • አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ለተቋም የሰው ሀብት ሥራ አመራርን የተመለከቱ መመሪያዎች እንዲከለሱና አዳዲስ ጥናት እንዲጠኑ ያደርጋል፣ የጥናት ውጤቶችን ይገመግማል፣
  •  ለሥራ መደቦች የሥራ ትንተና ተከናውኖ የሥራ ዝርዝር መግለጫ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣
  • መልካም ተሞክሮዎችን በማጣጣም ዳይሬክቶሬቱ የሚመራበትን አዳዲስ አሰራሮች በመቀመር እንዲቀመር በማድረግ፣ በመገምገም የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፣ ያስፋፋል፤
  • የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ ሰርኩላሮችና አግባብነት ያላቸው መመሪያዎችን ተፈጻሚነታቸውን ይከታተላል፣
  •  በተቋም ውስጥ ሜሪቲን የተከተለ የሰው ሀብት ምልመላና መረጣ እንዲከናወን ያደርጋል፣
  • በተቋም ውስጥ ልዩ ልዩ ጥቅማ ጥቅሞችና አገልግሎቶች ሳይዛቡ ሥራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፣
  • ደረጃውን የጠበቀ የሰው ሃብት የሥራ አካባቢ ደህንነትና ጤንነት ጥበቃ እንዲከናወን ያደርጋል፣
  • የሠራተኛ የግል ማህደሮች ተሟልተውና ዘመናዊ ሆነው እንዲያዙ ክትትል ያደርጋል፣
  • በተዋረድ ከሚገኙ ተቋማት  በሰው ሃብት ሥራ አመራር ዙሪያ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች የአሠራር ሥርዓቱን መሠረት በማድረግ ምላሽ እየሠጠ ፣ አፈፃፀሙን  ይገመግማል፣ትክክለኛነቱን ያረጋግጣል፣ 
  • የሰው ኃይል እቅድ መረጃዎች እንዲሰበሰቡ፣ እንዲደራጁ ተተንትነው እንዲጠናቀሩ ያደርጋል፣ የመረጃዎችን ትክክለኝነት ያረጋግጣል፣ ለሚመለከተው አካል ያስተላልፋል፣
  • በደረጃው ለተፈቀዱ የስራ መደቦች የሰው ኃይል ስምሪት ፈተናዎችን ያዘጋጃል፣ በሚመለከታቸው የስራ ክፍሎችም እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ ይፈትናል፣ እንዲፈተኑ ያደርጋል፣ ያርማል፣ እንዲታረም ያደርጋል፣ መረጃዎቹን በዘመናዊ የመረጃ ዘዴ /በሃርድና በሶፍት ኮፒ/ ተደራጅተው እንዲያዙ ያደርጋል፣
·      በዞንና በወረዳ የተሟላ የሰው ኃይል ቅጥር፣ ዝውውርና ምደባ ህጋዊነት በማረጋገጥ ማስተካከያ በማደረግ ትክክለኛነቱን ያረጋግጣል፣